ethiox.com
ethiox.com
Donate!
web hosting service
SELECT command denied to user 'kcgvincw_fusion1'@'localhost' for table 'fusion_site_links'
Latest Links

  


  


  


  


  

Search

Enter Keywords:


ለማጣፈጫ ሃገርን ወረራ!
Amharicለማጣፈጫ ሃገርን ወረራ!

በ1600ኛው መቶ ዓመታት ውስጥ የኢንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች በምዕራብ ኢንደስ (West Indies) እግራቸውን ሲያሳርፉ አላማቸው ትንበሆና ጥጥ ለሃገራቸው ፋፍሪካዎች ለማቅረብ ነበር። ከነዚህ ደሴቶች ከሆነቸው ባርባዶስ (Barbados) ላይ ከአረፉት ቀኝ ገዥዎች አንዱ ጄሚስ ዳራክስ (James Drax) የሚባለው በብራዚል ሃገር ሸንኮራ እንደሚሆን ካየ በኋላ በዚች ደሴት ላይ 1655 ዓ ም የሸንኮራ ተከላ ጀመረ።

ተልኮውን ለማጣፈጫ ፍላጋ( needs for sweeter) በሚል ሰየመው። የሸንኮራ አገዳ ተከላ ለማጣፈጫ ፍለጋ ለምዕራብ ኢንዲስ (West Indies) ወይም በአሁኑ መጠሪያቸው ለካረቢያን (Caribbean) ሃገሮች መጥፊያቸው ሆነ። ሃገሬው ከአጽም ርዕስቱ ተነቀለ። ያለ ክፍያ በቀለብ ብቻ ለቀኝ ገዥዎቹ በሸንኮራ ተከላውና ቆረጣው ላይ ተሰማራ። ቀኝ ገዥዎች የሃገሬው ጉልበት አልበቃ ብሏቸው አተላንቲክ ውቂያኖስን አቆርጠው ሩብ ሚሊዮን የሚሆኑትን አፍሪካውያንን ለባርነት ወደ ካረቢያን ሃገሮች እንደቃ በሰንሰለት ቀርቅበው በመርከብ ጭነው አመጧቸው።

በባርባደሰ (Barbados) የተጀመረው የሸንኮራ ተካላ ወደ ጃሜካ (Jamaica) ሊዋርደ ደሲቶች (Leeward Islands) ተሰፋፋ። የኢንግሊዝ ዜጎች ከቀድሞ አባቶቻቸው የሰኳር ፍጆታ በስድስት ጊዜ ጨመረ። የካረቢያን (Caribbean) ሃገሮች መሬታቸውን አጡ፤ ባህል አልባ ሆኑ፤ የማንነት መገለጫው ዘፈንና ሩጫ ሆነ። ዛሬ በርስታቸው ላይ ሰፍረው የሚገኙት በባርነት ለሸንኮራ ተከላና ቆረጣ የመጡት አፍሪካውያን ናቸው።

ወደ ኋላ ተመልሰን ከአፍሪካ በባርነት ሰም የመጡቱን አፍሪካውያን ሁኔታ ስናየው እጅግ የሚሰቀጥጥ ነው። ትንሽ ጥፋት ካጠፉ ወይም ከበደሉ የተነሣ ለማመጽ ከተነሣሱ አለቀላቸው።ውኃና ምግብ ተነፍገው እንዲሞቱ ይደረጋሉ፤ የደከመው ሰውነታቸው ለውሻ ይቀርባል፤ እዚህ ከመድረሳቸው በፊት በእግር ብረት ይታሰራሉ፤ ይገረፋሉ፤ አካለ ሥንኮላን እንደሆኑ ይደረጋል። የዚህ ሁሉ መነሻው የሰኳር ምርትን አሳድጎ ባለሐብቱ ተደላቆ እንዲኖር የኢንግሊዝም ሕብረተሰብ የሰኳር እጥረት እንደይፈጠርበት ነበር።

በአሁንም ዘመናችን (Caribbean Sugar industry taken as a model of international exchange) በማለት ይወደሳል። ይታያችሁ በካረቢያ ሕዝቦች ላይ ለስኳር ተከላ ሲባል ሃገር አልባ የሆኑትን እንደጥሩ ምሳሌ ይጠቀሳል።እህጉራዊ ንግድ (Globalization trade) የሚባለው ምስጢሩ ይህ ነው።

መለስ ዜናዊም እንደጌቶቹ የኢትዮጵያ ገበሬ ከቀደሞ ይልቅ አሁን የሰኳር ተጠቃሚ ሆኗል አያለ በማሰብ ችሎታችን ላይ ያሾፋል። በገልባጩ ገበሬውን ከርዕስቱ አየነቀለ በሕጋዊነት ሕገወጥ ተግባር እየፈጸመ ይገኛል። እስከ መቼ ይቀጥላል?

በነፃነቷ ኮርታ በጅግኖች ልጆቿ ተከብራ ቅኝ ገዥዎችን አሣፍራ የኖረች ሃገራቸን በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በአህጉራዊ ንግድ (Globalization) ስም ተደፍራለች። ዘርን መሠረት ያደረገው በትግራይ ክፍለ ሃገር በስልሳዎቹ ዓመተ ምህረቶች እንቅስቃሴ የጀመረው ቡድን ኢትዮጵያን ለባዕዳን ከበርቴዎች ለስያጭ አቅርቧታል።
የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ኢትዮጵያ በማስተዳደር ስም ለባዕዳን ሃገሪቱን እየሸጠ ይገኛል። ምንም አንኳን አንድ ሃገር ላዕላዊነቷን የሚያስጠበቅ የመከላከያ ኃይል ቢኖራትም የኢትዮጵያ ሠራዊት ለዚህ በቂ ሆኖ አልተገኘም። ለባዕዳን ጥቅም አስጠባቂ መሆኑን በጋንቢላ፣ በዋልድባ፣ በአፍር፣ በኦጋዴን፣በአርሲ፣ በወለጋ፣ በከፋ፣ በሻኪሶ መሬታችን ለሸኮራ ተከላ ለባዕድን አይሰጥንም በማለታቸው በሃገሬቱ ሰም የተዋቀረው የመከላከያ ኃይሉ በአጋዚ ሠራዊት ሰም ሕዝቡን እያጠፋ ነው።

የወቅቱ መንግሥት በቁንጮው መለስ ዜናዊ የሚመራው የትግራይን ልጆች በዘር ሐረጋቸው አታሎ፤ ከተራ ወታደር እስከ ጅንራል በሚደርስ የማዕረግ እርከን ፤ ከእግር ጠፍራቸው እስከ ፀጉር ጫፋቸው አስታጥቆ በአጋዚ ስም መሬቴን ለባዕዳን አሣልፌ አልሰጥም ያለውን ሕዝብ ያስጨርሳል።ይህ ሠራዊት ማሰብ ያለበት በእፍሪካኖችና በካረቢያን (Caribbean)ሃገሮች ላይ የደረሰውን ዓይነት ውርደት በልጅ ልጆቹ ላይ እንደሚደርስ ከአሁኑ መገንዘብ አለበት። በዘር አሻክላ ወጥመድ ተተብትቦ በማዕረግና በጥቅማጥቅም ተወጥሮው ዛሬ ቢታይ መጭው ትውልድ ያፍርበታል። የልጅ ልጆቹ ሲወቅሱት ይኖራሉ። የሚታየውን አላየሁም ብሎ ቢክድ ደግሞ የቆም ሞት ነው።
ወታደሩ ሴቪሉም ተማሪው መምህሩ መላው የሃገሬ ሕዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሃገራችን ላይ በልማት ስም ያጃበበውን የውርደት ስንቅ ነገ ዛሬ ሳንል ማስቆም አለብን። የወያኔ ልማት ይዞ የሚመጣው ውርደት ነው፤ በአፍጫችን ይውጣ። ድማቸውን እያፈሰሱ ያሉት ወገኖቻችን ለልጅ ልጆቻችን መሆኑን ተረድተን አብረናቸው እንቁም። በካረቢያን ሃገሮች የደረሰው ውርደት እንደይደርሰብም መነሣቱ ዛሬ ነው።


ስው በሃገሩ
ሰው በወንዙ
ቢበላ ሣር ቢባላ መቅመቆ
ይከበር የለም ወይ! ማንነቱ ታውቆ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ከውርደት በቆራጥ ልጆቿና በእግዚሐብሔር ኃይል ትድናለች!

ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca


posted on 0 Comments · 5751 Reads · Print
Comments
No Comments have been Posted.
Post Comment
Please Login to Post a Comment.
Ratings
Rating is available to Members only.

Please login or register to vote.

No Ratings have been Posted.
Special Links

Login
Username

PasswordNot a member yet?
Click here to register.

Forgotten your password?
Request a new one here.
Latest Articles
Ethiopia(ጋ&#48...
Manipulating Aid
An Ethiopian Scholar...
Somali Investment in...
Message from Maakelawi
Search

Enter Keywords: