አላምጦ የመትፋት ፖሊሲ

Wednesday, 14 June 2017 12:59

በመሐሪ በየነ

 

የጭነት መኪናዎቸ ያለማቋረጥ ተፈጥሮ የለገሰቸውን አንጡራ ሀብት መሸከፍ የዕለት ተዕለት ተግባር ከሆነ ውሎ አድሯል። በየካ ክፍለ ከተማ ልዮ ስሙ ጨፌ ኦሮምያ ጣፎ ተብሎ  የሚጠራው አካባቢ ተመሳቅሏል። ቅጥ አንባሯ የጠፋ ስፍራ መባሉ ያን ያክል የተጋነነ አያስብለውም። ይልቁንስ እግዚያብሔር ሰማይን ያለካስማ ምድርን ያለምሶሶ ከፈጠረ በሀላ ተረፈ ምርቱን አባ ኪሮስ ኮንዶኒየም ጀርባ ባለው ከተማ  ቀመስ ገጠር እንዲራገፍ ያዘዘ ይመስል አባጣ ጎርባጣ መልካም ምድራዊ ገፅታ እንድትላበስ ተገዳለቸ።


ጭብጥ ለማትሞላ የከተማ ጎጆ ለመቀለስ በሚል አባዜ የግንብና ድንጋይ ከከርሰ ምድሪቷ መንግሎ በማውጣት ህልቆ መሳፍርት የሆነውን ርስት እንድታጣ የ40 ቀን ዕድሏ ከሆነ ዘመን ተቆጠረ።ሜዳ ሸንተረር የነበረው ቀየ ዛሬ  ዛሬ ከወትሮ በተለየ መልኩ እንደበሬ ሻኛዎች አርቲ ቡርቲ ተብለው በተፈረጅ የለም አፈር ክምሮቸና የድንጋይ ቁልሎቸ ተሰድራለቸ።


እነዚህ የጭነት መኪናዎች የሚያልፉበት መንገድ ከምድሪቷ ከፈለቁና ከዝናቡ ወጨፎቸ ከመነጬ ደም በለበሱ የውሃ ዝረቶቸ ተጥለቅልቃለቸ ቢባል ከእውነት የራቀ ምልከታ አይመስለኝም። እነዚያ የውሃ ዝረቶቸ በኮረብታማው የተራራ ጉባ ተሰንስለው ለተመለከተው ሀይቅ ይመስላሉ።


በብሉይ ዘመን እንደሚነገረው ተፈጥሮ ያመፀቸ ለት እግዚያብሔር ተቆጥቷል ተብሎ ይታሰብ ነበር። የተገላቢጦሽ ሆነና ነገሩ በአሁን ሰአት የሰው ልጅ የእግዚያብሔር ካባ ደርቦ በተፈጥሮ ላይ በእጅ ረጅሙ ዘመቻ ከፍቷል ያስብላል።


ለእርሻ የታዘዘው መሬት በአመት አንድ ጊዜ ቢበዛ ሁለቴ ብቻ ፍሬ ሊያፈራ እንዲፈረድበት የማደባሪያው ጦስ ለመሆኑ የለሙ አፈር መፈረካከስ አሳብቋል። ወደቀየው የሚያቀኑ ጥርጊያ መንገዶችም መጨቅየታቸው የአፈር መሸርሸር መበራከቱን ያመላክታል።


ቆላማውን ወበቅ በመመከት ነፋሻማ አየር የሚለግሱት ዛፎቸም ገሚሱ ተመንጥረው ገሚሱ ደግሞ በመስኖ ውሃ ማጣት ሳቢያ ጠውልገው እንኳን ለመንደሬው ነዋሪ እስትንፋስ ሊሆኑ ይቅርና ለራሳቸውም ሳይበጅ እንዲቀሩ ዕጣፈንታቸው ሆኗል።


ሿ  ሿሿ ሿሿሿሿ የሚል ሀይለ ድምፅ በማሰማት ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ጉንበስ   ቀና በማለት ሰላም ለኪ  ለቤተክርስቲያን የሚሉ የሚመስሉ የዛፍ ዘለላዎቸ ረግፈው ዱብ  ዕዳ በሆነው አውሎ ንፋስ በመወሰድ በቅፅበት ከተራራ  ከዛፍናግሳንግስ ቅሪቶቸ ሲላተሙ ይስተዋላል። ቅርንጫፎቹ ረግፈው መነሻም    መድረሻም የላቸውም። አንዴ ሰከን ብለው ቁጢጥ ሲሉ  ሌላ ጊዜ ደግሞ እዚህም   እዚያም ይንፎለፎላሉ። ጎጆ አልባ ቅርንጫፎቸ ሆኗል።


አጤ ምኒሊክ ዳግማዊ ከአውስትራሊያ  ያመጡት ባህር ዛፍ ቀርቶ በቀለማት በተንቆጠቆጡ የባህር ዛፍ  ዝርያ ዙሪያ   ገባው  ተዳርሶ እያደር  አዲስ ሆኖ አንድ ስንዝር እንኳን ዕድገት አይታይበትም። ዛሬም   ነገም ቁጥቋጦነቱን ማንም አይነጥቀውም። 


የሣር   የእንጨትና ጭቃ ዳሶች በቆርቆሮ  ተሽቀርቅረው ነፀብራቃዊ ጮራቸውን ሲለግሱ ላስተዋለ አንዳችም ምታሃታዊ ሃይል አጎናፅፈው ምድር ገነት ናት የሚባለውን የሖው ምስክሮቸ እምነት ተጋርተው ሳይወዱ  በግድ እንዲቀበሉ ግፊት ይጭራል። ለፅሎት በአንቅሮ ወደ ላይ ማንጋጠጡን ቀርቶ የመብራት ማማ አይኖዎን በመቀሰር ታምራዊ ምልክትን እንዲቋምጡ ያስችሎታል።


እንደአቅሚቲ እንኪ አርቲ በሚል ቀበሌና የአነጋገር ዘይቤ በመላበስ ይመስል ምስኪን አባወራ ጎጆአቸውን በቆርቆሮ በመወደር የባለቤታቸውንና የልጆቻቸውን የአይን መነፅር እጣሪያው ላይ በመለጎም እንደኮንዶሚኒየሙ እንዳይቀስሩ ተፍ   ተፍ ሲሉ ይስተዋላሉ።


ቤተክርስቲያኒቱም ብትሆን ጠበሏ ተነፍጓት ለልማት ተነሺ እንድትሆን ታዞባታል። ለልማት በሚል እሳቤ ድንጋይ የሚጠርቡት አፍላ ጉልበት ያላቸው ወጣቶቸ ድንጋዮን በመናጥ ደፋ  ቀና ይላሉ። 


በዘልማዳዊ መሣሪዎች ማለትም መዶሻ  አካፋ  መብሻ መቧጠጫና መሰነጃ ታግዘው ላስተዋለ እንደሶምሶም የፊልስጤም ግንብ ለመናድ የሚራወጡ ይመስላል። የጀርመን ግንብ ለማፍረስ የሚያብሩ ይመስላል። በእነዚህ የስራ መስክ የተሰማሩት ወንዶች  ብቻ ሲሆኑ ያውም በሙት አንጅታቸው  የተጠረበውን ድንጋይ ያጓግዛሉ። ሆድ መሙያ የዕለት እንጀራቸውን ተመግበው ወደስራው ያቀናሉ። አፍላ ጉልበታቸውን በጤና መታወክ ካላጡ በስተቀር መስራታቸውን አንዴ እንኳን ለአፍታ ገታ አያደርጉም።


በርግጥ ብዕሬን እንዳነሳ የገፋፋኝ ይህም አልነበር። ይልቁንስ የኦሮሞ ህዝብ ማንነቱን የሚወክለውን ዋርካ ዛፍ መና ቢስነት አሳስቦኝ ነው። ዋርካ ዛፍ የኦሮሞ ህዝብ መገለጫ ብቻ ሳይሆን የመላው ህዝብ ብርቅዪ የሰብል ዝርያዎቸ ጭምርም ናቸው። ታሪካዊና መንፈሳዊ ዳራም አላቸው። 


በጣፎ አካባቢ መታዘብ እንደቻልኩት አብዛኖቹ የዋንዛ የዋርካናየሾላ ዛፎች ህልውናቸው አጠያያቂ ለመሆን እየተቃረቡ ነው። ለምን ቢባል የተጠረቡ ድንጋዮቸ ተመንግለው የሚወጡት የዛፎቹን ስር ታክከው ስለሆነ ነው። ይባስ ብሎ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ምሶሶዎቸ የከተሙት ዛፎቹን ተገን ያደረጉ ስለሆነ ዛፎቹ እንዲኮሰምኑና የአፈር መሸርሸር ሰለባ እንዲሆኑ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥረዋል። በተለይ አባቶቸ በዛፎቹ በመጠለል ያከናወኑት የነበረውን የአፈርሳታ መርሐግብር እንዲሰናከል ሳንካ ሊሆን ቸሏል። ለምንቢባል እንደእኔ ምልከታ ማስፈራሪያ አዘል ቃል በኤሌክትሪክ ምሶሶ ሰለተተየበ ነው። 


በጥቅሉ እንዲህ አይነት ጉልበት ብዝበዛ  ተፈጥሮ የመቧጠጥ ሱስ ለአገር በቀል የሰብል ዝርያና ለወግ    ስርአት ክብር አለመስጠት አላምጦ የመትፋት ፖሊሲ ገዥው ፓርቲ እያቀነቀነ እንደሆነ እማኝ አያሻም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
252 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 941 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us