ኢሰመጉ የምርጫ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ ያደርጋል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ኢሰመጉ የምርጫ ሪፖርቱን ዛሬ ይፋ ያደርጋል

Postby መታፈሪያ » Thu Oct 27, 2005 7:27 pm

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢስመጉ) ምርጫ 97ን አስመልክቶ ያዘጋጀውን የምርጫ ትዝብት ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ እንደሚያደርግ ገለጸ። ኢሰመጉ በዚሁ ሪፖርቱ ምርጫው ፍትሐዊ አልነበረም ብሏል።

የሶማሌ ክልልን ምርጫ ጨምሮ 1500 ምርጫ ታዛቢዎችን በ1200 ምርጫ ጣቢያዎች ያሰማራው ኢስመጉ ዛሬ የተጠቃለለ የምርጫ ሪፖርቱን እንደሚያቀርብ ዋና ፀሀፊው አቶ አዳም መላኩ ገልጸዋል።

የኢሠመጉ ዋና ጸሀፊ እንደሚሉት በሪፖርቱ ማጠቃለያ የግንቦቱ ምርጫ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ አልነበረም የሚል መደምደሚያ ቢኖርም ምርጫ ቦርድን አስመልክቶ አጠቃላይ አስተያየት አልሰጠም።

23 ገፅ ባለው የምርጫ ሪፖርት በ30 ነጥቦች በምርጫው ወቅት አጋጠሙ የተባሉ ችግሮች ተዘርዝረዋል።

በሪፖርቱ የምርጫ ችግሮች ከተባሉት መካከል የምርጫ ካርድ ካልያዙ ሰዎች በተደጋጋሚ መምረጥ፣ የምርጫ ውጤት ላይ አልፈርምም ማለትና መንጠቅ፣ ታዛቢዎችን ማስፈራራት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ገለልተኛ ያለመሆን፣ የኮሮጆ እና የቁልፍ መጥፋትና መበላሸት፣ ከምርጫ ሕጉ ውጪ የቀበሌ አስተዳደሮች ምርጫ አስፈጻሚ ሆኖ መገኘት፣ አስቀድሞ ምልክት የተደረገባቸው የድምጽ መስጫ ወረቀቶች መታደል፣ በቆጠራ ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎችን ማስወጣት እና ሌሎች የምርጫ ችግሮች ይገኙበታል።

አቶ አዳም የምርጫ ሪፖርቱ ሳይወጣ የዘገየው የሶማሌ ክልል ምርጫ ከሌላው በመዘግየቱና በሎጀስቲክ ችግሮች መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን በፍርሃት ምክንያት ዘግይታችኋል የሚሉ ወገኖች መኖራቸውን ተጠይቀው በአስተያየቱ እንደማይስማሙ ገልጸዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ አለመስማቱን በተመለከተ በሪፖርቱ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ውጭ ቦርዱን አስመልክቶ በሪፖርቱ የተሰጠ አስተያየት አለመኖሩንም ዋና ፀሀፊው ተናግረዋል።

ከሪፖርተር ጥቅምት 16 ቀን 1998
መታፈሪያ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Thu Aug 28, 2003 11:53 pm
Location: ethiopia

Postby የዘመኑ ልሳን » Thu Oct 27, 2005 7:31 pm

Please ከወያኔ ጋዜጦች ላይ ዜና ነው ብለህ አታምጣብን::ጋዜጣቸው እንዲሸጥ ትራሽ ሰብስበው ስለሚጽፉ እንደቁም ነገር ይዘህ አትምጣብን::ዛሬ ያለው ትላንት ዕረቡን ነበር የታለ እስካሁን የወጣ::ልክም ይሁን አይሁን ከወያኔጋዜጦች ላይ ባታመጣ ደስተኞች ነን::
የዘመኑ ልሳን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2672
Joined: Tue Jun 07, 2005 7:16 am
Location: USA


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], ቢተወደድ1 and 6 guests